ከተከተቡ በኋላ

የሚከተለው መረጃ የካናዳ መንግሥትን እና ሌሎች የሳይንሳዊ እና የሕክምና ምንጮችን በመጠቀም በሕክምና ባለሙያዎች እና በሕዝብ ጤና ጉዳይ አዋቂዎች ለዚህ ድረ ገጽ ተዘጋጅቷል፡፡ እንደ አንድ የሕክምና ምክር ተደርጎ ሊወሰድ የታቀደ አይደለም፣ የኮቪድ-19 ን ክትባት አስመልክቶ ሊኖርዎት ስለሚችል ማናቸውም ጥያቄ ሁልጊዜ ብቃት ካለው የጠና እንክብካቤ አቅራቢ ምክር ይጠይቁ፡፡

በእርግጠኝነት መናገር አንችልም፣ ነገር ግን ክትባት ቢወስዱም እንኳ ቫይረሱን መሸከም ይችላሉ፡፡ ክትባቱ ሰዎች በቫይረሱ እንዳይታመሙ እንደሚከላከል ግን እናውቃለን፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳን ክትባትዎን ቢወስዱም አሁንም ቫይረሱን ተሸክመው ለሌሎች አስተላላፊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሂደት ውስጥ ክሊኒካዊ ሙከራዎች እየቀጠሉ ሲሄዱ፣ እንዲሁም የእውነተኛው-ዓለም ማስረጃዎች ብቅ እያሉ ሲመጡ የበለጠ እንማራለን፡፡ እስከዚያው ግን ጭምብሎቻችንን መልበስ መቀጠል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ያስፈልገናል፣ እንዲሁም በቂ የካናዳውያን ቁጥር ሙሉ በሙሉ እስኪከተቡ ድረስ የሕዝብ ጤና ምክሮችን መከተል መቀጠል ያስፈልገናል፡፡

ከክትባቱ በኋላ ሰውነት የመከላከል አቅሙን ለመገንባት ከሁለተኛው ዶዝ በኋላ ሁለት ሳምንታት ያህል ይወስዳል፡፡ አንድ ሰው ከክትባቱ በፊት ወይም ልክ ክትባቱን እንደ ወሰደ በቫይረሱ ሊጠቃ እና ሊታመም ይችላል፤ ምክንያቱም ክትባቱ መከላከያ ለመስጠት በቂ ጊዜ አልነበረውምና፡፡

በዚህም ምክንያት ነው ሙሉ ተከታታይ ሁለት ክትባቶች መውሰድ የሚያስፈልገው፡፡

ከመጀመሪያው ዶዝ (80-92%) በኋላ የኮቪድ-19 ክትባቶች የመጀመሪያ ውጤታማነት ቀድሞውኑ በጣም ከፍተኛ ነውና ቢያንስ ለጥቂት ወራት ይቆያል፡፡

ከአንድ የመድሃኒት መጠን በኋላ ከሌሎች ባለብዙ-መጠን ክትባቶች ጋር የሚከሰት ተሞክሮ የሚያመለክተው የማያቋርጥ መከላከያ ለስድስት ወር ወይም ከዚያ በላይ ሊቆይ ይችላል። በእውነቱ፣ ረዘም ላለ ጊዜ በሚጠብቁበት ጊዜ ሁሉ የተሻለ ማጠናከሪያ የበሽታ መከላከያ ምላሽ እንደሚያገኙ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል። ስለዚህ ይህ በሳይንስ የተደገፈ ነው።

እና ለአብዛኞቹ ክትባቶች፣ የፀረ-እንግዳ ህዎስ ደረጃዎች (የበሽታ መከላከያ) ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚወርዱ ሲሆን በድንገት ከመከላከያ ደረጃዎች በታች አይወድቁም። ከወራት ወይም ከዓመታት በኋላም ቢሆን፣ ሌላ የክትባት መጠን ረዘም ያለ የመከላከያ ጊዜን በመስጠት ከፍተኛ ወደሆኑ ደረጃዎች የበሽታ መከላከያዎችን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።

አሁን በካናዳ በጣም አስተማማኝ የክትባት አቅርቦት ስላለን፣ በመድሃኒት መጠኖች መካከል ያለው የጊዜ መጠን ወደ ስምንት ሳምንታት ቀንሷል።

አዎ፣ ለአሁኑ፣ የካናዳ የህዝብ ጤና ኤጄንሲ ጭምብልን እና ርቀት መጠበቅን ለማስወገድ ትክክለኛ ጊዜ መቼ እንደሆነ እስኪያረጋግጥ ድረስ። ይህ የሆነበት ምክንያት ክትባቱ ውጤታማ እስኪሆን (የበሽታ መከላከያ ለመገንባት) ብዙ ሳምንታትን ስለሚወስድበት እና በተቻለው ያህል ለብዙ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ መከላከያ የሚደረሰው የፋይዘር-ባዮኤንቴክ፣ የሞደርና እና የአስትራዜኔካ ኮቪድ-19 ክትባቶች ሁለተኛው መጠን ከተጠናቀቀ በኋላ ብቻ ነው።

ለተከተቡ ሰዎች መከላከያው ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ገና በውል አናውቅም፡፡ በ ኤም አር ኤን ኤ ክትባቶች የተደረጉ ጥናቶች በአሁኑ ወቅት የሚያሳዩት ክትባት የተሰጣቸው ሰዎች ቢያንስ ለስድስት ወራት ያህል ለኮቪድ-19 በጣም ጠንካራ የመከላከል አቅም እንደሚኖራቸው ነው፡፡ የበሽታ መከላከያ ለጥቂት ጊዜ የሚቆይ ይመስላል፣ ነገር ግን ጥናቶች ይህንን በጊዜ ሂደት ውስጥ መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡

የበሽታ መከላከያ አንድ ዓመት ይቆይ ወይም አሥር ዓመት ይሁን፤ ወይም በተወሰነ ጊዜ የማጠናከሪያ ክትባት የሚያስፈልግ እንደ ሆነ በአሁኑ ጊዜ እርግጠኞች አይደለንም፣

የኮቪድ-19 ክትባትን ተከትሎ ሰውነት መከላከያን ለመገንባት አብዛናውን ጊዜ ጥቂት ሳምንታት ይወስዳል፡፡ ነገር ግን ከፋይዘር-ባዮኤንተክ፣ ሞደርና እና አስትራዘነካ የኮቪድ-19 ክትባቶች እጅግ በጣም ጥሩ መከላከያ ለማግኘት ሁለቱ ዶዞች እንደሚያስፈልጉ ያስታውሱ፡፡ የጆንሶን እና ጆንሶን የኮቪድ-19 ክትባት አንድ ዶዝ ብቻ ይፈልጋል፡፡

ከክትባት በኋላ ጊዜያዊ ቀላል ወይም መካከለኛ የጎንዮሽ ጉዳቶች መኖራቸው የተለመደ ነው፡፡ እነዚህንም ይጨምራል፦

  • ሕመም፣ መቅላት፣ ሙቀት፣ መርፌ በተወጉበት ቦታ ማሳከክ፣ ወይም እብጠት፣
  • ድካም
  • ራስ ምታት
  • ማቅለሽለሽ
  • የጡንቻ ወይም የመገጣጠሚያ ሕመም፣ እንዲሁም
  • መለስተኛ ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት፣

እነዚህ ሰውነትዎ መከላከያ እየገነባ መሆኑን የሚያሳዩ የተለመዱ ምልክቶች ናቸው፡፡ እንዲሁም እነዚህ ምልክቶች በጥቂት ቀናት ውስጥ መሄድ አለባቸው፡፡

ምልክቶችዎ እየከበዱ ወይም እየተባባሱ ከሆኑ፣ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያማክሩ፡፡ ከኮቪድ-19 ጋር የሚገጥሙ ከሆነ፣ ምርመራ ማድፍረግና የምርምራ ውጤቶችንም እስኪያገኙ ድረስ ራስዎን ማግለል ይኖርብዎታል፡፡

በጣም ባልተለመደ መልኩ አናፍላክሲስ የሚባለው በጣም የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም በጠቃላይ ከተከተቡ በኋላ በብዙ ደቂቃዎች ውስጥ ወይም በመጀመሪያው ሰዓት ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት የኮቪድ-19 ክትባታቸውን የሚወስዱ ሰዎች ቢያንስ ለ 15 ደቂቃዎች እንዲቆዩ ይጠየቃሉ፡፡ በዚህም የጤና ጥበቃ ሠራተኖች ከባድ የሆነ የጤና ቀውስ ምላሽ ምናልባት ቢታይ ግለሰቦች ላይ ክትትል ለማድረግ ነው፡፡

የጎንዮሽ ጉዳቶች ክትባቱ እየሠራ መሆኑን ወይም አለመሆኑን የሚያመለክቱ አይደሉም፡፡

የጎንዮሽ ጉዳቶች ክትባቱ እየሠራ መሆኑን፣ ሰውነትዎም መከላከያ እየገነባ መሆኑን የሚያሳዩ የተለመዱ ምልክቶች መሆናቸው እውነት ነው፡፡ ሆኖም ይህ ማለት የጎንዮሽ ጉዳቶች ከሌሉዎት መጨነቅ አለብዎት ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ የኤም አርኤንኤ ክትባቶች በክሊኒካዊ ሙከራዎች ውስጥ ከ90% በላይ ለሆኑ ተቀባዮች የበሽታ መከላከያ ጥበቃን ሰጥተዋል፡፡ ነገርግን ከ50% በላይ የሆኑት ምንም የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላሳዩ ተናግረዋል፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ብዙ ሰዎች ምንም ዓይነት ግብረመልስ አላገኙም፣ ነገር ግን ሙሉ መከላከያ ነበራቸው ማለት ነው፡፡

ስለዚህ፣ ከኮቪድ-19 ክትባት በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት የማይሰማዎት ከሆነ የሚያስጨንቅ ነገር አይደለም —የጎንዮሽ ጉዳት ካጋጠመው ሰው ጋር አሁንም ተመሳሳይ ጥበቃአለዎት፡፡