ከመከተብዎ በፊት

የሚከተለው መረጃ የካናዳ መንግሥትን እና ሌሎች የሳይንሳዊ እና የሕክምና ምንጮችን በመጠቀም በሕክምና ባለሙያዎች እና በሕዝብ ጤና ጉዳይ አዋቂዎች ለዚህ ድረ ገጽ ተዘጋጅቷል፡፡ እንደ አንድ የሕክምና ምክር ተደርጎ ሊወሰድ የታቀደ አይደለም፣ የኮቪድ-19 ን ክትባት አስመልክቶ ሊኖርዎት ስለሚችል ማናቸውም ጥያቄ ሁልጊዜ ብቃት ካለው የጠና እንክብካቤ አቅራቢ ምክር ይጠይቁ፡፡

አዎ፣ ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች አሁንም በሁለት የመድሃኒት መጠኖች ሙሉ በሙሉ መከተብ አለባቸው። ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ ለምን ያህል ጊዜ እንደገና ከመታመም እርስዎ እንደተጠበቁ ባለሙያዎች ገና አያውቁም። ክትባት በሽታ ሳያጋጥምዎት የፀረ-እንግዳ ህዎስ ምላሽ በመፍጠር እርስዎን ለመጠበቅ ይረዳዎታል።

በቅርብ ጊዜ ኮቪድ-19 ይዞት ከነበረ፣ ጥሩ ስሜት እስኪሰማዎት ድረስ እና ክትባቱን ከመቀበልዎ በፊት ራስን-የማግለል ጊዜዎ እስኪያበቃ ድረስ መጠበቅ አለብዎት።

የ MRNA ክትባትን (ፋይዘር-ባዮኤንቴክ ወይም ሞደርና) እንደ የመጀመሪያ የመድሃኒት መጠንዎ ከወሰዱ፣ እንደ ሁለተኛ የመድሃኒት መጠንዎ የ mRNA ክትባት ይሰጥዎታል። በቀላሉ የማይገኝ ወይም የማይታወቅ ካልሆነ በቀር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወስደው የነበረውን ዓይነት ክትባት ቢወስዱ ተመራጭ ነው፣ በዚህ ጊዜ ሌላውን የ mRNA ክትባት ዓይነት መውሰድ ችግር የለውም። ሁለቱም እኩል ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ ናቸው።

አስትራዜኔካን እንደ የመጀመሪያ የመድሃኒት መጠንዎ ከወሰዱ፣ አስትራዜኔካን እንደ ሁለተኛ የመድሃኒት መጠንዎ ለመውሰድ መምረጥ ይችላሉ፣ ነገርግን NACI ለሁለተኛ የመድሃኒት መጠንዎ የ mRNA ክትባትን እንዲወስዱ እየመከረ ነው።

በካናዳ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ሁሉም ክትባቶች ሆስፒታል መተኛትን እና ከባድ ህመምን በእኩል እና በብቃት የሚቀንሱ፣ ሲሆን ሁሉም በኮቪድ-19 የተነሳ ሞት እንዳይከሰት ለመከላከል 100% ያህል ውጤታማ ናቸው።

አስፈላጊው ነጥብ ለሙሉ መከላከያ በሁለት መጠኖች ክትባት ለመውሰድ መጠበቅ የለብዎትም። ብዙዎች ታማሚ እንዲሆኑ፣ ሆስፒታል እንዲተኙ እና ለሞት እንዲዳረጉ የሚያደርጉ አዳዲስ የቫይረስ ዓይነቶች ብቅ እያሉ ሲሆን ይህንን ለማስቆም የጅምላ ክትባት ብቸኛው መንገድ ነው።

ክትባቱን የወሰደ ማንኛውም ሰው ሁሉ አሁንም የሕዝብ ጤና መመሪያን መከተል ይኖርበታል፡፡ ክትባት ከወሰዱ በኋላ እጅን መታጠብን ጨምሮ፣ ጤናማ የአካል ርቀትን መጠበቅ፣ ጭምብል ማጥለቅ፣ እንዲሁም ሕመም ከተሰማዎት ቤት መቆዬትን የመሳሰሉትን የመከላከያ እርምጃዎችን መለማመዱን መቀጠል አሁንም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ አስፈላጊ የሚሆንባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፣ ከእነዚህም፦
ሰውነትዎ ከኮቪድ-19 ክትባት መከላከያ ለማግኘት ቢያንስ ሁለት ሳምንታት ይወስዳል፡፡ ይህ ማለት ክትባቱን ከመውሰድዎ በፊት በኮቪድ-19 ከተያዙ፣ ወይም ክትባቱን ከወሰዱ በሁለት ሳምንቱ ጊዜ ውስጥ፣ አሁንም በኮቪድ-19 ቫይረስ ሊታመሙ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከተከተቡ በኋላ የኮቪድ-19 ምልክቶች ከተሰሙዎት ይመርመሩ፡፡
ክትባቱ ሁሉም ሰው ኮቪድ-19 ን እንዳያገኝ አያግደውም፡፡ ነገር ግን በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች በካባድ ሕመም የመያዙ ዕድላቸው እጅግ አነስተኛ ይሆናል፡፡
ያሉት ክትባቶች በጣም ውጤታማ ናቸው፣ ነገር ግን እርስዎ በሽታን የመከላከል አቅም ከሌላቸው አነስተኛ ቁጥር ሰዎች ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በአቅራቢያ ካሉ ሰዎች ጋር የሚገናኙ ከሆነ ወይም የሕዝብ የጤና እርምጃዎችን የማይከተሉ ከሆነ አሁንም ኮቪድ-19 ን ማሰራጨት ይችላሉ፡፡

አይደለም፡፡ የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የኮቪድ-19 ን ክትባት መውሰድ አለመውሰድ የእርስዎ ምርጫ ነው፡፡

ሁሉም የካናዳ ኗሪዎች፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምንም ለኮቪድ-19 ክትባት ብቁ ናቸው፡፡ ሕጋዊ የሆነ ፒኤችኤን (PHN) የግድ ሊኖርዎ አያስፈልግም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ብቁ የሆኑት ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉ ሞደርና፣ አስትራዘነካ እና ጆንሶን እና ጆንሶን ክትባቶችን ለመውሰድ ብቁ ናቸው፡፡ ዕድሜያቸው 12 ዓመት ዕድሜ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑት የፋይዘር – ባዮኤንቴክ ክትባት ለመውሰድ ብቁ ናቸው፡፡