የሚከተለው መረጃ የካናዳ መንግሥትን እና ሌሎች የሳይንሳዊ እና የሕክምና ምንጮችን በመጠቀም በሕክምና ባለሙያዎች እና በሕዝብ ጤና ጉዳይ አዋቂዎች ለዚህ ድረ ገጽ ተዘጋጅቷል፡፡ እንደ አንድ የሕክምና ምክር ተደርጎ ሊወሰድ የታቀደ አይደለም፣ የኮቪድ-19 ን ክትባት አስመልክቶ ሊኖርዎት ስለሚችል ማናቸውም ጥያቄ ሁልጊዜ ብቃት ካለው የጠና እንክብካቤ አቅራቢ ምክር ይጠይቁ፡፡
የክትባት መዝገብዎ በክፍለ ሀገርዎ ወይም በክልልዎ የጤና አገልግሎት ባለሥልጣን ዘንድ ይቀመጣል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ የኮቪድ-19 ክትባት መዝገብ በተመለከተ የጽሑፍ/ ወይም የኤሌክትሮኒች ቅጅ ለእርስዎም ይሰጣል፡፡ ምን ዓይነት ሰነድ እንደሚሰጥ ለመረዳት በክትባት ክሊኒክ ውስጥ ወይም በአካባቢዎ ያለውን የጤና አገልግሎት ባለሥልጣን እባክዎን ያነጋግሩ፡፡
አዎ፣ በክትባቱ ሂደት ውስጥ የሚመራዎ ረዳት ሰው ከፈለጉ፣ ወይም የቋንቋ ትርጉም ድጋፍ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ከእርስዎ ጋር አንድ ሰው ማምጣት ይችላሉ፡፡
የቀጠሮዎ ማረጋገጫ [ሰነድ] በወረቀት የታተመ ወይም የኤሌክትሮኒክ ቅጅ ይዘው መምጣት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ካለዎት የጤና ካርድዎን ይዘው መምጣት አለብዎት