የሚከተለው መረጃ የካናዳ መንግሥትን እና ሌሎች የሳይንሳዊ እና የሕክምና ምንጮችን በመጠቀም በሕክምና ባለሙያዎች እና በሕዝብ ጤና ጉዳይ አዋቂዎች ለዚህ ድረ ገጽ ተዘጋጅቷል፡፡ እንደ አንድ የሕክምና ምክር ተደርጎ ሊወሰድ የታቀደ አይደለም፣ የኮቪድ-19 ን ክትባት አስመልክቶ ሊኖርዎት ስለሚችል ማናቸውም ጥያቄ ሁልጊዜ ብቃት ካለው የጠና እንክብካቤ አቅራቢ ምክር ይጠይቁ፡፡
የጸረ ኮቪድ-19 ቫይረስ ክትባት መውሰድ በኮቪድ-19 እንዳይጠቁ ወይም እንዳይሞቱ ይረዳዎታል፡፡ እንዲሁም በካናዳ ውስጥ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለማስቆም፣ ቫይረሱ በማሕበረሰብ ውስጥ እንዳይዛመት ለመቆጣጠር በቂ ቁጥር ያላቸው ካናዳውያን መከተብ ይኖርባቸዋል፡፡
አንድ ሰው ምንም እንኳ በኮቪድ-19 ባይሞትም የማስታወስ ችሎታን መቀነስ፣ ድካም፣ ለመግለጥ የሚያስቸግር የመተንፈስ ችግር፣ እንዲሁም በሳንባና በልብ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ጨምሮ ሌሎች የረዥም ጊዜ እክሎች ሊያጋጥሙት ይችላሉ፡፡
በቂ የሰዎች ቁጥር የበሽታ መከላከያ ካላቸው ቫይረሱ የመዛመት እድሉ አነስተኛ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የመንጋ መከላከያን ለማግኘት እና ወደ ዕለታዊ ኑሮአችን ለመመለስ፣ የንግድ ሥራ ቦታዎች እንደገና ለመክፈት፣ የምንወዳቸውን ሰዎች እንደገና ለማዬትና ለማቀፍ ቢያንስ እስከ 75% የሚሆነው ሕዝብ መከተብ ይኖርበታል፡፡
የለም፣ ሁሉም የኮቪድ-19 ክትባቶች በነጻ ናቸው፡፡
በጁን-አጋማሽ ላይ፣ የክትባት ብሔራዊ አማካሪ ኮሚቴ (NACI) ለሁለተኛ የክትባት መጠኖች የኮቪድ-19 ክትባቶች መለዋወጥን በተመለከተ ምክሮቻቸውን አዘምነዋል። ከዚህ የተደባለቀ የክትባት መርሃግብር የተሻለ በሽታ የመከላከል አቅም ምላሽ ሊኖር በሚችል በተገለፀ ማስረጃ ላይ በመመርኮዝ፣ የ mRNA ክትባት አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ የአስትራዜኔካ የመድሃኒት መጠን ላገኙ ግለሰቦች እንደ ሁለተኛው የመድሃኒት መጠን ይመረጣል።
የ MRNA ክትባትን (ፋይዘር-ባዮኤንቴክ ወይም ሞደርና) እንደ የመጀመሪያ የመድሃኒት መጠንዎ ከወሰዱ፣ እንደ ሁለተኛ የመድሃኒት መጠንዎ የ mRNA ክትባት ይሰጥዎታል። በቀላሉ የማይገኝ ወይም የማይታወቅ ካልሆነ በቀር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወስደው የነበረውን ዓይነት ክትባት ቢወስዱ ተመራጭ ነው፣ በዚህ ጊዜ ሌላውን የ mRNA ክትባት ዓይነት መውሰድ ችግር የለውም። ሁለቱም እኩል ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ ናቸው።
አስትራዜኔካን እንደ የመጀመሪያ የመድሃኒት መጠንዎ ከወሰዱ፣ አስትራዜኔካን እንደ ሁለተኛ የመድሃኒት መጠንዎ ለመውሰድ መምረጥ ይችላሉ፣ ነገርግን NACI ለሁለተኛ የመድሃኒት መጠንዎ የ mRNA ክትባትን እንዲወስዱ እየመከረ ነው።
በካናዳ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው ሁሉም ክትባቶች ሆስፒታል መተኛትን እና ከባድ ህመምን በእኩል እና በብቃት የሚቀንሱ፣ ሲሆን ሁሉም በኮቪድ-19 የተነሳ ሞት እንዳይከሰት ለመከላከል 100% ያህል ውጤታማ ናቸው።
አስፈላጊው ነጥብ ለሙሉ መከላከያ በሁለት መጠኖች ክትባት ለመውሰድ መጠበቅ የለብዎትም። ብዙዎች ታማሚ እንዲሆኑ፣ ሆስፒታል እንዲተኙ እና ለሞት እንዲዳረጉ የሚያደርጉ አዳዲስ የቫይረስ ዓይነቶች ብቅ እያሉ ሲሆን ይህንን ለማስቆም የጅምላ ክትባት ብቸኛው መንገድ ነው።
በካናዳ ጤና አገልግሎት ቢሮ (Health Canada) ጥናት መሠረት እና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ክትባት የሚወስዱትን ያሳተፉ ክሊኒካዊ ሙከራዎችን መሠረት፦
ፋይዘር-ባዮኤንቴክ ሁለት ዶዝ ከተወሰደ በኋላ 95% ውጤታማ ነው፡፡
ምንጭ፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/pfizer-biontech.html
ሞደርና ሁለት ዶዝ ከተወሰደ በኋላ 94% ውጤታማ ነው፡፡
አስትራዘኒካ ከሁለት ዶዝ በኋላ 62% ውጤታማ ነው (በሰሜን / ደቡብ አሜሪካ ጥናቶች መሠረት 79%)
የሪል ዎርልድ ጥናት እንደሚያመለክተው ደግሞ ኤዜድ ሆስፒታል ተኝቶ መታከምን በመከላከል ከ80-90% ውጤታማ ነው፡፡
ምንጭ፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/astrazeneca.html
ጆንሶን እና ጆንሶን ከአንድ ዶዝ በኋላ 66% ውጤታማ ነው፡፡ እንዲሁም የሪል ታይም ጥናታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ከባድ ህመምንና ሆስፒታል መተኛትን በመከላከል >90% ውጤታማ ነው፡፡
ምንጭ፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/janssen.html
ስለሆነም አራቱ ክትባቶች ከባድ የኮቪድ-19 ጥቃትን፣ ሆስፒታል መተኛትንና መሞትን በመከላከል በጣም ውጤታማ ናቸው፡፡
ይህ በእርግጥ በክትባቶች እና በተለዋዋጭ ዓይነቶች መካከል ይለያያል፡፡
እያንዳንዱ የኮቪድ-19 ክትባት በአሁኑ ጊዜ በካናዳ ውስጥ እይተዛመቱ ካሉት ማናቸውም ተለዋዋጭ ዓይነቶች ከባድ ህመምን / ሞትን ይከላከላል፡፡
በተወሰኑ ዝርያዎች ላይ ዝቅተኛ ውጤታማነት የሚያሳዩ ክትባቶች እንኳን በእነዚህ አዳዲስ ዓይነቶች ላይ በተሻለ ሁኔታ ለመሥራት አምራቾቹ የክትባቶቻቸውን አዲስ ስሪቶች እየፈጠሩ ነው፡፡ ስለሆነም በሚቀጥሉት ወራትና ዓመታት ውስጥ ውጤታማ የሚሆነውን የመቋቋምን አቅም ከፍ የሚያደርጉትን ክትባቶች ማግኘት ምናልባት ትችሉ ይሆናል፡፡
ለፋይዘር-ባዮኤንቴክ፣ሞደርና እንዲሁም አስትራዘኒካ ሁለት ዶዝ መውሰድ ያስፈለገበት ምክንያት የመጀመሪያው ዶዝ ሰውነትዎ የመከላከል አቅም ምላሽ እንዲሰጥ ይበልጥ “ያዘጋጀዋል”፦ ሰውነትዎ ኮቪድ-19 ን ለመዋጋት ጸረ-እንግዳ ህዋስ አካላትን ማዘጋጀት ይማራል፡፡ ሁለተኛው ዶዝ ደግሞ ለጠንካራ እና ረዘም ላለ ጊዜ የመከላከል አቅም እንዲኖረው “ያጠናክረዋል”፡፡ የበሽታን ሙሉ ተከላካይነት አቅም ለመስጠትም ሁለቱም ዶዞች ያስፈልጋሉ፡፡
የጆንሶን እና ጆንሶን ክትባት ተሞክሮአል እናም በአንድ ዶዝ ብቻ ሰዎችን የመጠበቅና በሽታን የመከላከል አቅማቸውን የማሳደግ ውጤት አሳይቷል፡፡
ፋይዘር-ባዮኤንቴክ እና ሞደርና፦ ኤምአርኤንኤ ክትባቶች
የኮቪድ-19 ን ዛላ የሚሠራ ጥቃቅን የኤምአርኤንኤ ፕሮቲን በሴሎችዎ ውስጥ ይገባና የኮቪድ-19 ን ቫይረስ የሚቋቋሙ ጸረ-እንግዳ ሕዋስ አካላትን እንዲፈጥር ሰውነትዎን ያስተምረዋል፣ ከዚያም ኤምአርኤንኤው መመሪያዎችን በሰውነትዎ ውስጥ ወደኋላ በመተው እርሱ ራሱ በሰዓታት ውስጥ ይጠፋል፡፡
አስትራዘነካ እና ጀይ እና ጀይ፦ የቫይረስ ፍላጻ ክትባቶች፣
እነዚህ ክትባቶች ጉዳት የሌለው ቫይረስ፣ የተዳከመ (እንደ ጉንፋን ቫይረስ ዓይነት) ይጠቀማሉ፤ ከዚያም የኮቪድ-19 ቫይረስ ቁራጭ ፕሮቲን ተጨምሮበት ይሻሻላል፡፡ ይህም ሰውነታችን ጸረ እንግዳ ህዋስ አካላትን እንዲሠራ ያደርጋል፤ እንዲሁም ሌሎች በሽታን የመከላከል የሚጠቅሙ ሴሎችን ያነቃቃል፡፡
አንዳቸውም ቢሆኑ ከእርስዎ ዘረ-መል (ዲ ኤን ኤ) ጋር አይገናኙም ወይም አይቀይሩም!
አንዳቸውም ህያው የሆነ የኮቪድ-19 ቫይረስ አይይዙም፡፡
ሁሉም ተመሳሳይ የጎንዮሽ ተጽእኖዎች ይኖራቸዋል፦ ይህም መርፌ በሚወጉበት ቦታ የሕመም ስሜት፣ ድካም፣ ትኩሳት ወይም የጉንፋን ዓይነት ምልክቶች፣ ራስ ምታት፣ ቀላል የጡንቻ / የመገጣጠሚያ ሕመም፣
የካናዳ ጤና አገልግሎት ፋይዘር-ባዮኤንቴክ፣ ሞደርና፣ አስትራዘነካ እንዲሁም ጆንሶን (ጆንሶን እና ጆንሶን) የኮቪድ-19 ክትባቶችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ አጽድቋል፡፡
የለም፡፡ የኮቪድ-19 ን ክትባት ጨምሮ ማንኛውም ክትባት መውሰዱ ህያው ክትባት ስላልሆነ በኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖረውም፡፡