ክትባት፣ ጤና እና ደህንነት

የሚከተለው መረጃ የካናዳ መንግሥትን እና ሌሎች የሳይንሳዊ እና የሕክምና ምንጮችን በመጠቀም በሕክምና ባለሙያዎች እና በሕዝብ ጤና ጉዳይ አዋቂዎች ለዚህ ድረ ገጽ ተዘጋጅቷል፡፡ እንደ አንድ የሕክምና ምክር ተደርጎ ሊወሰድ የታቀደ አይደለም፣ የኮቪድ-19 ን ክትባት አስመልክቶ ሊኖርዎት ስለሚችል ማናቸውም ጥያቄ ሁልጊዜ ብቃት ካለው የጠና እንክብካቤ አቅራቢ ምክር ይጠይቁ፡፡

በክልልዎ ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባቱን ለመውሰድ ብቁ ስለ መሆንዎ እያሰቡ ከሆነ፣ ወይም የኮቪድ-19 ክትባቱን ለማግኘት ቀጠሮ ለመያዝ ከፈለጉ ለሚኖሩበት አካባቢ በጣም ወቅታዊ መረጃ እና የቦታ ማስያዝ አማራጮችን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን አገናኝ ጠቅ ያድርጉ፡፡

ብሪትሽ ኮለምቢያ
አልበርታ
ሳስኬችዋን
አኒቶባ
ኦንታሪዮ
ኩዊቤክ
ኒው ብራንዝዊክ
ኖቮ ስኮሻ
ኒው ፋውንድላንድ እና ላብራዶር
ፕሪንስ ኤድዋርድ አይላንድ
ኖርዝዌስት ተሪቶሬስ
ኑኑቩት
ዩኮን

በካናዳ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀደላቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች እንቁላል፣ ጀላቲን፣ የአሳማ ሥጋ፣ የላቸውም፣ የበሬ ሥጋ፣ የጽንስ ውጤቶች፣ ሜርኩሪ፣ ፎርማልዳይድ፣ አሉሚኒየም፣ ቲሜሮሳል፣ ወይም ላቴክስ የላቸውም፣ እንዲሁም በምግብ ወይም ሃይማኖታዊ ምክንያቶች የተከለከሉ ነገሮች የሏቸውም፡፡
ለእያንዳንዱ ክትባት የተሟላ ንጥረነገሮች ዝርዝር ከዚህ በታች ይገኛል፦

ፋይዘር-ባዮኤንቴክ፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/pfizer-biontech.html

ሞደርና፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/moderna.html

አስትራዘነካ፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/astrazeneca.html

ጆንሶን እና ጆንሶን፦ https://www.canada.ca/en/health-canada/services/drugs-health-products/covid19-industry/drugs-vaccines-treatments/vaccines/janssen.html

ምንም የተዘለሉ ደረጃዎች የሉም፤ እንዲሁም ሂደቱ ሁሉንም የደህንነት ሂደቶች የተከተለ ሲሆን ክትባቶቹ አሁን ባለው የቴክኖሎጂ እድገት ግስጋሴ ምክንያትና እንዲሁም ህክምና ነክ ያልሆኑ የማረጋገጫ ክፍሎች በፍጥነት ክትትል ስለ ተደረገባቸው ነው፡፡

የለም፡፡ በክትባቱ ውስጥ ያለው ፕሮቲን ከእርስዎ ዘረ መል ጋር ፈጽሞ አይገናኝም ወይም አይቀይረውም፡፡ ለኮቪድ-19 ከተጋለጡ ሰውነትዎ ጸረ እንግዳ ሕዋስ አካላትን እንዲሠራ የሚያዝዙ መመሪያዎችን ወደ ኋላ አስቀርቶ ክትባቱን በወሰዱ በሰዓታት ውስጥ በተፈጥሮአዊ ሂደት ራሱ ይደመሰሳል፤

የፋይዘር-ባዮኤንተክ ክትባት ከ12 ዓመት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ክልል ላሉ ልጆች እንዲሰጥ በካናዳ ጤና አገልግሎት ሚኒስትሪ ተፈቅዷል፡፡

የሞደርና፣ የአስትራዘነካ እና ጆንሶን እና ጆንሶን ክትባቶች ግን ዕድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ላሉ እንዲሰጥ ተፈቅዷል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቶች በትናንሽ ልጆች ላይ ደህንነትና ውጤታማነትን ለማወቅ በአሁኑ ሰዓት ጥናቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ጊዜ በካናዳ ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባቶች ከሌሎች ክትባቶች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ መሰጠት የለባቸውም፡፡ ሆኖም በአሜሪካ ውስጥ የየኮቪድ-19 ክትባቶች እና ሌሎች ክትባቶች አሁን ጊዜውን ከግምት ሳያስገቡ፣ በተመሳሳይ ቀን የኮቪድ-19 ክትባትዎን እና ሌሎች ክትባቶችን በአንድ ጊዜ መስጠትን ጨምሮ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ይህም ለእርስዎ እንደ ተገለጸ ከጤና አቅራቢዎ ጋር መወያየት አለብዎት፡፡

ምንም እንኳ በጣም ጥቂት ሰዎች ለክትባቱ አንዳንድ ክፍሎች በሚኖራቸው ከባድ የሰውነት ቁጣ ምላሽ (አለርጂዎች) ምክንያት ክትባቱን አለመውሰድ ቢኖርባቸውም፣ ሁሉም ሰዎች ማለት ይቻላል ክትባቱን በሚገባ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከኮቪድ-19 ቀጣይ አደጋ አንጻር ሲታይ፣ ብዙ ሰዎች ክትባት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ፣ መሠረታዊ የጤና ችግሮች ያሉባቸውና በክሊኒካዊ ሁኔታ በጣም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 ልክፈት ለሚመጡ ችግሮች የበለጠ ሊጋለጡ ይችላሉና ክትባቱ እንደ ደረሰላቸው ጊዜ ሳይወስዱ ወዲያውኑ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ፣ ከሕመም በማገገም ላይ ያሉ ቢሆንም እንኳ (ለምሳሌ፦ ነርቭ የሚያጠቃ በሽታ – ሺንግልስ) ለእርስዎ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ ጤናማ ነው፡፡ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴዎችን እንዳያከናውን የሚያግድዎ አዲስ ሕመም ካለብዎት እስኪያገግሙ ድረስ ክትባቱን ማቆዬት አለብዎት፡፡ ይህም ክትባቱ ሊያመጣ የሚችለውን እምቅ የጎንዮሽ ጉዳት ከሌላው ሕመምዎ መባባስ ለመለየት ይረዳል፡፡ እንዲሁም ከተላላፊ በሽታ እስኪያገግሙ ድረስ ይጠብቁ፡፡ ለክትባትዎ ሲመጡ ሌሎችን በበሽታው የመያዝ አደጋ ላይ እንደማይጥሉ ያረጋግጣል፡፡

የኮቪድ-19 ምልክቶች ካለዎት ቤት ውስጥ መቆየት እና ምርመራ ማድረግ አለብዎት፡፡

ሁሉም ሰው ማለት ይቻላል ክትባቱን በደህና መውሰድ ይችላል፣ ደካማ የሆነ የሰውነት በሽታን የመከላከል ስርዓት ወይም የራስን-ተከላካይ ህዋስ የሚያጠቃ በሽታ ላለባቸው ሰዎች ደህንነት ላይ ጉልህ ሥጋት የለባቸውም፡፡ የበሽታ መከላከያ አቅማቸው ደካማ በሆኑ ሰዎች ላይ ክትባቱ እንደ ታሰበው ላይሰራ ይችላል፡፡ ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እንዲሁም በሽታን የመከላከል አቅምዎ ከተዳከመ፣ ራስን የሚያጠቃ ተከላካይ በሽታ ከለዎት ስለ ኮቪድ-19 ጉዳይ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ወይም ሃኪምዎን ያነጋግሩ፡፡

የወር አበባ ውስብስብ የሆነ ሂደት ያለው ነውና በብዙ ነገሮች አማካይነት ተጽእኖ ሊደርስበት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፦ አካባቢያዊ ለውጦች፣ ጭንቀት፣ እንቅልፍ እና አንዳንድ መድኃኒቶች፡፡ በእርግጥ ማኅጸን ውስጥ ያለው ሽፋን በሽታን የመከላከል ስርዓት የያዘ ንቁ አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ክትባት በመውሰድዎ ወይም በመታመምዎ ምክንያት የሰውነትዎ በሽታን የመቋቋም አቅምና ሥርዓት ተጠናክሮ ሲሰራ ውስጠ-ማኅጸን (ኢንዶመትሪዩም) ምላሽ በሚሰጥበት ጊዜ ለውጦች ሊያጋጥሙዎት ይችላሉ፡፡ በዚህ መንገድ ክትባቱ በወር አበባ ላይ በመጠኑ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡

ነገር ግን ልብ ሊባልለት የሚገባው አንድ ነገር አለ፡፡ እርሱም በማንኛውም የብዙ ሰዎች ስብስብ በሚታዩበት ጊዜ ብዙ በወር አበባ ዑደት ውስጥ ለውጦች የሚያጋጥሟቸው አንዳንድ ሰዎች ሁልጊዜ አሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ በመቶ ሚልዮን የሚቆጠሩ ክትባቶች እየተሰጡ ባሉበት በዚህ ጊዜ በወር አበባቸው ተፈጥሮአዊ ኡደት ላይ ለውጦች የሚከሰቱባቸው አንዳንድ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ በወር አበባ ኡደት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦች ላይ ስጋት ሊኖር እንደሚገባ የሚጠቁም በቂ መረጃ ባለ መኖሩ ተመራማሪዎች ክትባቱ ደህና ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ ክትባቱ እያደር አይለወጥም፣ ስለሆነም በቅርቡ ክትባት በወሰዱ ግልሰቦች ዙርያ መገኘት በአንድ ሰው ኡደት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡

ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ በወር አበባዎ ዑደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ማናቸውም ለውጦች ጊዜያዊ ናቸው፣ ስለዚህ የክትባቱን መርፌ ላለመወጋት ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ የሚያሳስብ ነገር ያላቸው ሴቶች ዑደቶቹ በሌሎች ምክንያቶችም ሊዘገዩ ስለሚችሉ ከሐኪማቸው ጋር መነጋገር ይኖርባቸዋል፡፡

የካናዳ የጽንስና የማሕጸን ሕክምና ማሕበር (SOGC)፣ ብሔራዊ የክትባት አማካሪ ኮሚቴ፣ እንዲሁም በካናዳ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች ሁሉም እርጉዝ ወይም ጡት የሚያጠቡ ሴቶች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ እንዲሁም በማናቸውም ጊዜ ክትባት ሊሰጣቸው (በማናቸውም ሦስትዮች ወራት)፣ በእርግዝና ወቅት፣ እንዲሁም ጡት በማጥባት ወቅት ብቁ ከሆኑ እና ምንም ዓይነት ተቃርኖዎች እስከሌሉ ድረስ ክትባት ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እንዲሁም እርጉዝ ከሆኑ፣ ለማርገዝ በእቅድ ላይ ከሆኑ፣ ወይም ጡት በማጥባት ላይ የሚገኙ ከሆነ ስለ ኮቪድ-19 ክትባት ጉዳይ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ፡፡

የኮቪድ-19 ክትባትን ጨምሮ ማንኛውም ክትባት በሴቶችም ሆነ በወንዶች የመራባት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ምንም ዓይነት ማስረጃ የለም፡፡

አንድ ሰው የኮቪድ-19 ክትባቱን የማይወስድባቸው በጣም ጥቂት የሆኑ ምክንያቶች አሉ፡፡

ስለሆነም በሚከተሉት ምክንያቶች ክትባቱን መውሰድ የለብዎትም፦

1. በክትባቶቹ ውስጥ ላሉት ማናቸውም ንጥረ ነገሮች ከባድ አለርጂ ቢኖርዎት፦ በኤምአርኤንኤ ክትባቶች ውስጥ ያለ አንድ ንጥረ ነገር አልፎ አልፎ ከከባድ አለርጂ (አናፊላክሲስ) ጋር የተያያዘ ፖሊቲሊን ግላይኮል (ፒኢጂ) የሚባል ነው፤ ይህም በአንዳንድ ማስዋቢያ ኬሚካሎች፣ የቆዳ እንክብካቤ ምርቶች፣ የሚያስቀምጥ መድኃኒት፣ በአንዳንድ በፋብሪካ በተመረቱ ምግቦች እና መጠጦች ውስጥ እና ሌሎች ምርቶች ውስጥ ይገኛል፡፡ ማስታወሻ፦ ፒኢጂ በአስትራዘነካ ክትባትና በጆንሶን እና ጆንሶን ክትባቶች ውስጥ የለም፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከበድ ካለ አለርጂ ጋር የተያያዘ በአስትራዘነካ እና ጆንሶን እና ጆንሶን ክትባቶች ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር ፖሊሶርቤት 80 የሚባለው ነው፡፡ በሕክምና መድኃኒቶች ቅመማ ዝግጅትም ውስጥ ይገናል (ለምሳሌ፦ የባይታሚን ዘይቶች፣ ክኒኖች እንዲሁም የጸረ ካንሰር መድኃኒቶች) እና የውበት ኬሚካሎች ውስጥ ይገኛል፡፡

2. ከዚህ በፊት ከተሰጠዎት የኮቪድ-19 ክትባት ዶዝ ጋር ወይም ከክትባቱ ማንኛውም ክፍል ጋር የተያያዘ ለሕይወት አስጊ የሆነ ተቃራኖ እክል ካጋመዎት፣

አደገኛ የአናፊላክቲክ እክል ውጤት ካጋጠምዎት ነገር ግን መነሻ ምክንያቱን ካላወቁት የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ፡፡ ለክትባቶቹ ከባድ፣ ለሕይወት አስጊ የሆኑ የአለርጂ ምላሾች (አናፊላክሲስ) እጅግ በጣም አናሳ ናቸው – ሰዎች ከሚያስቡት በጣም ያነሰ፡፡ አናፊላክሲስ በሁሉ ሁኔታ መከላከል የሚቻል ነው፣ በሁሉም ሁኔታም ሊታከም የሚችል ነው፡፡ በካናዳ ውስጥ ክትባትን በመስጠት የሚሠሩ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ሁሉ ስልጠና እንዲሰጣቸው ያስፈልጋል፡፡ እንዲሁም ወዲያውኑ አናፊላክሲስን በንቃት መከታተል እና ማከም እንዲችሉ፣ አልፎ አልፎ በአለርጂ ሐኪም እና በሕክምና ጤና መኮንን ምክሮች ላይ በመመርኮዝ፣ አንድ ሰው በሆስፒታል መሰናዶ ውስጥ ክትባት መውሰድ ይችላል፡፡

አልኮል እንዲጠጡ ወይም ወደ ክትባት ቀጠሮዎ ሰክረው እንዲመጡ አይመከርም፡፡ ይህም ክትባቱ አሳሳቢ የሆነ የጤንነት ስጋት ስላለው (አልኮል በክትባቱ ላይ ጣልቃ ይገባል ማለት) ሳይሆን ነገር ግን የጤና እንክብካቤ አቅራቢው ባለሙያ ክትባቶችን ለእርስዎ ከመስጠቱ በፊት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ስምምነትዎን ይፈልጋልና፡፡ አልኮሆል የጤና መረጃውን ሙሉ ለሙሉ የመረዳት፣ እንዲሁም ተገቢ ጥያቄዎችን የመጠየቅ ችሎታዎን (ሊያሳንስ) ይችላል፡፡

በአልኮል አጠቃቀም እና በኮቪድ-19 ክትባቶች ውጤታማነት ዙሪያ ምንም የተደረጉ ጥናቶች የሉም፡፡ ከአልኮል አጠቃቀም ቀውስ (AUD) ጋር የሚታገሉ ሰዎች ያላቸውን በሽታን የመከላከል አቅም (ያዳክማል) ያኮስሳልና የጤና አቅራቢ ባለሙያን ያነጋግሩ፡፡ የባለሙያ አስተያየት እንደሚጠቁመው መጠነኛ የሆነ መጠጥ በክትባቱ የበሽታ መከላከያ ምላሽ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ብለን አንጠብቅም፡፡

ካናቢስ የሚጠቀሙ ከሆነ የኮቪድ-19 ክትባቱ ለእርስዎ ጤናማነት የተጠበቀ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የቀጠሮዎ ጊዜ ሲደርስ (በዕጽ መጠቀም ምክንያት) ከፍ ባለ ስሜት ሆነው እንዳይመጡ እንመክራለን፡፡ ይህም ስንል (መሪዋና በክትባቱ ላይ ጣልቃ እንደሚገባ) በክትባቱ ደህንነት አሳሳቢ ስጋት ስላለ አይደለም፡፡ ነገር ግን የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ባለሙያ ክትባቶችን ለእርስዎ ከመስጠቱ በፊት በዕውቀት የተደገፈ ስምምነትዎን የሚፈልግ በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡ መሪዋና ደግሞ የጤና መረጃውን ሙሉ በሙሉ የመረዳት እና ጥያቄዎችን የመጠየቅ ችሎታዎ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ስለሚችል ነው፡፡

በካናቢስ አጠቃቀምና በኮቪድ-19 ክትቫቶች ውጤታማነት ዙሪያ የተደረገ ምንም ዓይነት ጥናት የለም፡፡ ካናቢስ ማጨስ በሰው የመተንፈሻ አካላት አሰራር ላይ እና በሽታን የመከላከል ብቃቱ ላይ አሉታዊ መዘዞችን ሊያስከትል እንደሚችል አዳዲስ መረጃዎች ብቅ እያሉ ናቸው፡፡ እንዲያውም የሚያጨሱ ከሆነ ራስዎን ከቫይረሱ ለመጠበቅ የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡